ሐጅ

የሐጅ ትርጉም

ሐጅ ማለት የተወሰኑ አምልኮት ተግባራትን ለመፈፀም ወደተከበረው አላህን ማምለኪያ ቤት-በይቱላሂል ሐራም(ካዕባ) በማሰብ መጓዝ ነው፡፡ ከዚያም፣ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላለፉ ተግባሮችና ንግግሮችን ማከናወን ነው፡፡ ኢሕራም መታጠቅ፤ በካዕባ ዙሪያ ሰባት ጊዜ መዞር፤ በሠፋና በመርዋ ኮረብታዎች መሐል ሰባት ጊዜ መመላለስ፤ በዐረፋ መቆም፤ በሚና ጠጠሮችን መወርወርና ሌሎችንም ተግባራት መፈፀምን ያጠቃልላል፡፡

ሐጅ በውስጡ ለአላህ ባሮች ከበባድ ጥቅሞችን ይዟል፡፡ ከነኚህም ጥቀሞች መካከል፤ የአላህን አሃዳዊነት በይፋ ማሳየት፣ ሐጃጆች የሚጎናጸፉት ላቅ ያለ ምህረት፣ የሙስሊሞች መተዋወቅ፣ የሃይማኖት ድንጋጌዎችን በተግባር መማርና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡

የሐጅ ወቅት፡ የሐጅ ተግባራት የሚፈፀሙት ከዙልሒጃ ወር ስምንተኛው ቀን አንስቶ እስከ አስራ ሶስተኛው ቀን ድረስ ነው፡፡ ዙልሒጃ፣ በጨረቃ ቀመር (ኢስላማዊ አቆጣጠር) መሰረት አስራ ሁለተኛው ወር ነው፡፡

ሐጅ ግዴታ የሚሆነው በማን ላይ ነው?

ሐጅ ግዴታ የሚሆነው፣ በአንድ ለኃላፊነት በደረሰ ሙስሊም ላይ ሲሆን እርሱም የሚችል ከሆነ ነው፡፡

የመቻል ትርጉም

መቻል ስንል፡ ሕጋዊና ትክክለኛ በሆነ መንገድ ወደ በይተል ሐራም መድረስ መቻልና የሐጅን ሥርዓት ከተለመደው በጉዞ ላይ ከሚያጋጥም መንገላታት ውጭ ምንም ዓይነት መንገላታትም ሆነ ችግር ሳይገጥመው መፈፀም መቻል ነው፡፡ በተጨማሪም ለነፍሱና ለንብረቱ ዋስትና የሚኖረው መሆን፤ ለሐጅ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ለማሟት ወጪ የሚያደርገው ገንዘብ፣ መሰረታዊ ፍላጎቶቹን ከሚሸፍንበትና በርሱ ስር ከሚተዳደሩ ሰዎች ወጪ የተረፈ ሲሆን ነው፡፡

አንድ ሙስሊም ሐጅ ማድረግ የመቻል መገለጫዎች፡

 1. በራሱ ሐጅ ማድረግ መቻሉ፡ አንድ ሙስሊም፣ በቂ ገንዘብ ያለው ከሆነና ከተለመደው የጉዞ እንግልት በተጨማሪ ምንም ዓይነት እንግልት ሳይደርስበት በራሱ ወደ በይተል ሐራም መድረስ ከቻለ የግዴታን ሐጅ በራሱ የማድረግ ግዳጅ አለበት፡፡
 2. በራሱ ሳይሆን በሌላ ሰው ሐጅን ማስፈፀም የሚችል መሆኑ፡ ዕድሜው የገፋ አዛውንት በመሆኑ ወይም ህመምተኛ በመሆኑ ምክንያት ሐጅ ማድረግ የማይችል፣ ነገር ግን እርሱን ወክሎ ሐጅ ሊያደርግለት የሚችልን ሰው የሚያገኝ ከሆነና እርሱን ወክሎ ሐጅ እንዲያደርግለት ወጪውን መሸፈን ከቻለ፣ የወኪሉን ወጭ ሸፍኖ ሐጅ የማስደረግ ግዴታ አለበት፡፡
 3. በራሱም ሆነ በሌላ ሰው አማካይነት ሐጅ ማድረግ የማይችል፡ ይህ ዓይነቱ ሰው የማይችል እስከሆነ ድረስ ሐጅ የማድረግ ግዴታ የለበትም፡፡

ፍላጎቱን ከሚያሟላበትና የቤተሰቡን ወጪ ከሚሸፍንበት የሚተርፈው ሐጅ ሊያደርግበት የሚችል ምንም ዓይነት ገንዘብ የሌለው ሰው በምሳሌነት ይጠቀሳል፡፡

ሐጅ ማድረግ የሚያስችለው ገንዘብ ለማግኘት ገንዘብ የማሰባሰብ ግዴታ የለበትም፡፡ በቻለ ጊዜ ግን ሐጅ ግዳጅ ይሆንበታል፡፡

 አንዲት ሴት ሐጅ ለማድረግ መሕረም (የቅርብ ተጠሪዋ) አብሯት መኖሩ መስፈርት ነው፡፡

በሴት ላይ ሐጅ ግዴታ ሊሆን የሚችለው መሕረሟ (የቅርብ ተጠሪዋ) ካለ ብቻ ነው፡፡ መሕረሟ አብሯት ከሌለ በሴት ልጅ ላይ ሐጅ ግዴታ አይሆንም፡፡ ለአንዲት ሴት መሕረም የሚሆኗት ባለቤቷ ወይም እርሷን ፈፅሞ ማግባት የማይፈቀድላቸው፣ እንደ አባት፣አያት፣ልጅ፣የልጅ ልጅ፣ ወንድሞችና የወንድም ልጆች፣ አጎቶች፣ ….. (ገጽ 200 ተመልከቱ) ናቸው፡፡

በራሱዋ የምትተማመን ሁና ያለሙህሪም ሐጅ ካደረገች ሐጁዋ ትክክል ነው፤ ምንዳም ያስገኛታል፡፡

 • ሐጅ ለማድረግ የሚያበቃህ የሆነ በቂ ገንዘብና አካላዊ ብቃት
  • አዎን => በራስህ ሐጅ ልታከናውን ግዴታ ይሆንብሃል፡፡
  • አይቻልም(በፍፁም) => ሐጅ ለማድረግ በቂ ገንዘብ አለህ ነገር ግን ይድናል ተብሎ በማይከጀል ሕመም ምክንያት ሐጅ ለማድረግ የሚያስችል የአካል ብቃት የለህም፣አለያም በጣም ሸምግለሃል፡፡
   • አዎን => በዚህን ጊዜ አንተን ወክሎ ሐጅ ለሚያደርግ ሰው ወጪውን የመሸፈን ግዴታ አለብህ፡፡
   • አይቻልም(በፍፁም) => ከመሰረታዊ ፍላጎቶችህና በአንተ ስር ከሚተዳደሩ ሰዎች መሰረታዊ ወጪ የሚተርፍ የሆነና ሐጅ ለማድረግ የሚያስችልህ በቂ ገንዘብ ከሌለህ ሐጅ የማድረግ ግዳጅ የለብህም፡፡ ሐጅ ለማድረግ ገንዘብ ማስባሰብም አይጠበቅብህም፡፡