በረመዳን ጾሙን ያበላሸ ሰው ፍርዱ ምንድን ነው?

በረመዳን ጾሙን ያበላሸ ሰው ፍርዱ ምንድን ነው?

ማንኛውም ያለ በቂ ምክንያት ጾሙን ያበላሸ ሰው፣ ከባድ ወንጀል ፈጽሟል የፈጣሪውን ትዕዛዝ ጥሷል፡፡ ስለዚህም፣ በተውበት ወደ አላህ መመለስ ይኖርበታል፡፡ ጾሙን ያበላሸው በግብረ ስጋ ግንኙነት ካልሆነ፣ ከዚህ ከተውበቱ በተጨማሪ ያንን ጾም የፈታበትን ቀን መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ ጾሙን የፈታው በግብረ ስጋ ግንኙነት ከሆነ ግን፣ ያንን ቀን መክፈል፣ እንዲሁም ለሠራው ወንጀል ማበሻ፣ ባሪያን ነፃ ማውጣት አለበት፡፡ ይህም፣ ሙስሊም ባሪያን በመግዛትና ከባርነት በማላቀቅ ይተገበራል፡፡ እናስተውል! ኢስላም፣ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ለሰው ልጅ ከባርነት ቀንበር ነፃ መውጣት ትኩረት ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ አሁን እንዳለንበት ዘመን ዓይነት ባሪያን ነፃ ማውጣት የማይቻል ከሆነ፣ ሁለት ወሮችን በተከታታይ ይጾማል፡፡ ይህንንም ካልቻለ ስልሳ ሚስኪኖችን ያበላል፡፡