አምስቱ እጅግ አስፈላጊ ነገሮች

አምስቱ እጅግ አስፈላጊ ነገሮች፡-

 ተግባራችን ተገቢ ወዳልሆነ ተግባር ቢያሰማራንም የሰው ልጅን ነፍስ መጠበቅ እንደሚኖርብን አላህ አዞናል፡፡

እነዚህ አምስት ነገሮች ሰው ተገቢ በሆነ መልኩ ይኖር ዘንድ የሚያስፈልጉ ወሳኝ የሆኑ ጥቅሞች ናቸው፡፡ ለሁሉም መለኮታዊ ህግጋት የተደነገጉት እነዚህን ነገሮች ለመጠበቅና እነዚህን ተቃርነው የተገኙ ነገሮችን ለመከላከል ነው፡፡

እስልምና የተደነገገው፥ አንድ ሙስሊም ለዱንያዊ ሆነ አኼራዊ ህይወት በዚህ ዓለም ላይ ተረጋግቶ ይሰራ ዘንድ፥ እነዚህን አምስት ነገሮች ለመጠበቅና ለመንከባከብ ነው፡፡

ሙስሊሙ ህብረተሰብ የሚኖረው፥ እርስ በርሱ ተደጋግፎ እንደቆመ ግንብ በመተሳሰር ነው፡፡ አንዱ አካል ሲጎዳ ሌላውም ጉዳቱ በትኩሳትና በእንቅልፍ ማጣት እንደሚሰማው እንደ አንድ የሰውነት አካል ሆነው ይኖራሉ፡፡

 

ይህንኑ መጠበቅ የሚቻለው በሁለት መንገድ ነው፡-

በመገንባትና በመንከባከብ

  1. ሃይማኖት፡

ሃይማኖት ማለት አላህ ሰዎችን ለዚሁ ዓላማ ሲል የፈጠረበትና ታላቅ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ መልእክተኞች የላከውም ይህንኑ እንዲጠብቁ ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል… “በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ አላህን ተገዙ ጣዖትንም ራቁ በማለት መልእክተኛን በእርግጥ ልከናል…” (አል-ነሕል፡36) የሃይማኖትን ብፁዕነት የሚያቆሽሹና እንደ ሺርክ፣ ከንቱ እምነት፣ ወንጀልና ኃጢአት የመሳሰሉ ነገሮች ሃይማኖትን ለመጠበቅ ሲባል ኢስላም ተከላክሏቸዋል፡፡

  1. አካል፡-

ተግባራችን ተገቢ ወዳልሆነ ነገር ቢያሰማራንም የሰው ልጅን ነፍስ መጠበቅ እንዳለብን አላህ አዞናል፡፡ በአስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ እስከ ሆንን ድረስ አላህ ለእኛ ምህረትን ይለግሰናል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል… “… ሺፍታና ወሰን አላፊ ሳይሆን (ለመብላት) የተገደደ ሰውም በርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡” (አል-በቀራህ፡173)

የራስን ነፍስ መግደልና መጉዳትንም ከልክሏል፡፡ እንዲህ ይላል… “በአላህም መንገድ ለግሱ በእጆቻችሁም (ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ…” (አል-በቀራህ፡195)

የእስልምና ሃይማኖት አንድ ሰው የትኛውም ሃይማኖት ይከተል በሱ ላይ ድንበር እንዳይታለፍበትና ወንጀል እንዳንፈፅምበት በሚል ወሰኖችን አበጅቷል መቀጣጫ ህግጋትንም አኑሯል፡፡ እንዲህ ይለናል…«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተገደሉ ሰዎች ብድር መመለስ በናንተ ላይ ተጻፈ…» (አል-በቀራህ፡178)

  1. አዕምሮ፡-

አዕምሮ አላህ ከለገሳቸው ታላላቅ ፀጋዎች ውስጥ አንዱ በመሆኑ፥ እርሱን የሚጎዱና አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳርፉበትን ነገሮች እስልምና ከልክሎዋል፡፡ የሰው ክብርና ማንነት የሚገለፀው በርሱ ነው፡፡ በዚህ ዓለም (ዱንያ) ሆነ በቀጣዩ ዓለም አኼራ ሂሳቡን የሚያወራርደውና ጥያቄ የሚቀርብለት በርሱ ነው፡፡

ለዚህ ነው አላህ ማንኛውንም ዓይነት አስካሪ መጠጥና አደንዛዥ ዕፅን የከለከለው (ሃሐራም) ያደረገው ከፀያፍና ከሸይጣን ተግባራት ተርታ መድቦታል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የሚያሰክር መጠጥ፣ ቁማርና ጣዖታትም የመጠንቆያ እንጨቶች (አዝላምም) ከሰይጣን ስራ የኾኑ እርኩስ ብቻ ናቸው፤ እርኩስን ራቁትም ልትድኑ ይከጀላልና፡፡” (አል-ማኢዳህ፡90)

  1. ዘር፡-

የእስልምና ሃይማኖት ዘርን ለማስቀጠልና ለቤተሰብ ግንባታ ከፍተኛ ትኩረት የሰጠውና ጥበቃ ያደረገለት ነገር መሆኑ በተለያዩ መርሆቹና ህግጋቶቹ ውስጥ ጎልቶ ሲታይ ይስታዋላል፡፡ ከዚህ ውስጥ የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡-

  • የእስልምና ሃይማኖት ለትዳር በጣም ያበረታታል፡፡ ቀለል ባለ አኳኋን እንዲመሰረተም ይገፋፋል፡፡ ቅድመ ሁኔታዎቹ እንዳናካብዳቸውም ያዘናል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል “ከናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፡፡” (አል-ኑር፡32)
  • እስልምና ሕገ-ወጥ የሆኑ ማንኛውም ዓይነት የፆታ ግንኙነቶችን ከልክሎዋል፡፡ ወደ እርሱ የሚያደርሱ ጎዳናዎች ሁሉ ዝግ እንዲሆኙ አድርጓል፡፡ እንዲህ ይለናል፡፡ «ዝሙትን አትቅረቡ፤ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፤ መንገድነቱም ከፋ!» (አል-ኢስራእ፡32)
  • እስልምና የሰው ዘርና ክብር ማንቋሸሽና ማጥላላትንም በጥብቅ አውግዞዋል፡፡ ይህ መሰሉን ተግባር ከከባባድ ወንጀሎች ውሰጥ መድቦታል፡፡ ይህን ወንጀል የፈፀመ ሰው በአኼራ ከሚጠብቀው ቅጣት በተጨማሪ፤ ዱንያ ላይም ከባድ ቅጣት እንደሚጠብቀው አላህ አስጠንቅቋል፡፡
  • የወንድም ሆነ የሴት ልጅ ክብር እንዲጠበቅና እንዳይጣስ አዞዋል፡፡ የራሱንም ሆነ የቤተሰቦቹን ክብር ለማስጠበቅ ሲል የተገደለ ሰው በአላህ መንገድ እንደተሰዋ ሰማዕት ቆጥሮታል፡፡ (ገጽ፣ 196 ተመልከት)
  1. ገንዘብ፡-

ገንዘብ ጥበቃ ይደረግለት ዘንድ እስልምና ግዴታ አድርጓል፡፡ የዕለት ጉርስን ፍለጋ መንቀሳቀስንም እንዲሁ ከተለያዩ ሰዎች ጋር የሚደረግ የንግድ ግብይትና የቢዝነስ ልውውጥንም የተፈቀደ ተግባር አድርጎታል፡፡

ለገንዘብ ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል ከሚል እሳቤ በመነሳትም፥ አራጣን፣ ስርቆትን፣ ማታለልን፣ ማጭበርበርንና በሀሰት መንገድ የሰው ገንዘብ መብላትን ሓራም አድርጓል፡፡ እነዚህን የወንጀል ተግባራት የሚፈፅም ሰው፥ በቅዱስ ቁርኣን ከፍተኛ የሆነ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶታል፡፡