አደንዛዥ እጽ

አደንዛዥ እጽ

የሚበቅልም ይሁን በፋብሪካ የተመረተ አደንዛዥ እጽን በአፍንጫ በመሳብም ሆነ በመዋጥ፣ ወይም በመርፌ መልክ በመወጋት መጠቀም ወይም መውሰድ ከታላላቅ ወንጀሎችና ሃጢኣቶች መካከል ነው፡፡ እሱ አዕምሮን የሚጋርድ ከመሆኑም በተጨማሪ የሰው ልጅን ነርቮች ያበላሻል፡፡ አደንዛዥ እጽን የሚያዘወትር ሰው በተለያዩ የነርቭና የመንፈስ በሽታዎች ይጠቃል፡፡ ምናልባትም ለሞቱ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ነፍሶቻችሁንም አትግደሉ አላህ ለናንተ አዘኝ ነውና፡፡›› (አል ኒሳእ 29)