ኢስላማዊ አስተራረድ

ኢስላማዊ አስተራረድ

ኢስላማዊ መስፈርቶችን ያሟላ እርድ ማለት ነው፡፡

የኢስላማዊው አስተራረድ መስፈርቶች

  1. የሚያርደው ግለሰብ ለማረድ ብቃት ያለው መሆን አለበት፡፡ እሱም ሙስሊም ወይም የመጽሐፍት ባለቤቶችን፣ ክርስቲያንና አይሁዳውያንን የሚያካትት ሲሆን እርዱን መምረጥ የሚችልና ስለ እርድ የሚያውቅ መሆን አለበት፡፡
  2. የሚያርድበት መሳሪያ እንደ ቢላዋ ያለ የሚቆርጥ፣ ደም የሚያፈስና ለማረድ ብቃት ያለው መሆን አለበት፡፡ እንሰሳቱን በክብደቱ በሚጫን መሳሪያ፣ ወይም የእንሰሳቱን ጭንቅላት በመግጨት ወይም በኤሌክትሪክ ንዝረት በማቃጠል መግደል እርም ነው፤ አይፈቀድም፡፡
  3. እጁን ለማረድ በሚያንቀሳቅ ጊዜ ‹‹ቢስሚላህ›› በማለት የአላህን ስም ማውሳት፡፡
  4. በእርድ ላይ መቆረጥ ያለባቸውን ክፍሎች መቁረጥ፡፡ እነርሱም የአየር ቧንቧ፣ ጉሮሮና ሁለቱ የደም ጋኖች ናቸው፡፡ እነኚህ፣ በአንገት ግራና ቀኝ ያሉ የደም ስሮች ናቸው፡፡ ከነኚህ አራት አካላት መካከል ሦስቱን ቢቆርጥ በቂ ነው፡፡

እነኚህ ጉዳዮች ከተሟሉ እርዱን መብላት ይበቃል፡፡ ነገር ግን ከእነኚህ መስፈርቶች መካከል አንዱ ከተጓደለ እርሱን መብላት አይፈቀድም፡፡