እርሱ ሰልሞ ሚስቱ ባትሰልም የሚኖረው ድንጋጌስ ምንድነው?

በዚህ ጊዜ የሴቷ ሃይማኖት ግምት ውስጥ ይገባል፤ የመጽሐፍት ባለቤት፣ ማለትም አይሁድ ወይም ክርስቲያን ልትሆን ትችላለች፤ አለያም እንደ ቡድሂዝም ሂንዱዊዝምና ጣዖት አምላኪያን መጽሐፍት የለሽ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ልትሆን ትችላለች፤ ወይም በሃይማኖት የማታምን ሃይማኖት አልባ ልትሆንም ትችላለች፡፡ እና ፍርዱ ምንድን ነው?

 1. የመጽሐፍት ባለቤት ሃይማኖት ተከታይ የሆነች ሚስት

አንድ ሰው ቢስልምና ሚስቱ ግን ባትሰልም፣ የመጽሀፍት ባለቤት ሃይማኖት ተከታይ ብትሆን፣ የጋብቻው ውል በነበረበት ሁኔታ ይቀጥላል፡፡ ምክንያቱም አንድ ሙስሊም አንዲትን የመጽሐፍት ባለቤት ሃይማኖት ተከታይ ሴትን ቢያገባ አይከለከልም፡፡ ስለሆነም ይህም የሰለመ ሰው ከሚስቱ ጋር የጋብቻ ሕይወቱን መቀጠሉና በሚስትነት እሷን ይዞ መቆየቱ የተሻለ ነው፡፡

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ዛሬም መልካሞች ሁሉ ለናንተ ተፈቀዱ፤ የነዚያም መጽሐፉን የተሰጡት ሰዎች ምግብ (ያረዱት) ለናንተ የተፈቀደ ነው፤ ምግባችሁም ለነሱ የተፈቀደ ነው፤ ከምእመናት ጥብቆቹም ከነዚያ ከናንተ በፊት መጽሐፉን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፡፡›› (አል ማኢዳ 5)

ነገር ግን ባገኘው አጋጣሚና ብልሃት በመጠቀም እሷን ወደ እስልምና በመጥራቱ ላይ ከፍተኛ ጥረት ሊያደርግ ይገባል፡፡

 1. የመጽሐፍት ባለቤት ሃይማኖት ተከታይ ያልሆነች ሚስት

ሰውየው ሰልሞ ሚስቱ ኢስላምን ለመቀበል ባትሆንና በሃይማኖቷ የመጽሐፍቱ ባለቤት ተከታይ -አይሁድ ወይም ክርስቲያን- ባትሆንና ቡድሂስት ወይም ሂንዱዊስት ወይም ጣዖት አምላኪ ወይም የሌላ እምነት ተከታይ ከሆነች፡-

አንዲት ፍች ሴት የምትጠብቀውን ወቅት ያክል ይጠብቃል፡፡ ዝርዝሩ ከዚህ ቀጥሎ ባለው ክፍል ሰንጠረዥ ውስጥ ተጠቅሷል፡፡

 • በዚህ ቆይታ ውስጥ ከሰለመች ሚስትነቷ ይቀጥላል፡፡ የጋብቻውን ውል በአዲስ መልክ መፈፀም አያስፈልግም፡፡
 • ወቅቱ እስከሚያልቅ ድረስ ተጠብቃም ኢስላምን ለመቀበል ፍቃደኛ ካልሆነች ግን ጋብቻው ይፈርሳል፡፡

ከዚህ ጊዜ በኋላ ከሰለመችና ሊያገባት ከፈለገ እንደ አዲስ ለጋብቻ ያጫትና ያገባታል፡፡ አላህ ሱ.ወ እንዲህ ይላል፡- ‹‹የከሃዲዎቹንም ሴቶች የጋብቻ ቃል ኪዳኖች አትያዙ፡፡›› (አል ሙምተሒናህ 10) ከሰለማችሁ በኋላ ከመጽሐፍት ባለቤት ሌላ የካሃዲያንን ሴቶች በጋብቻ ቃል ኪዳኖች አትያዙ ማለት ነው፡፡

የተፈታች ሴት ዒዳ (ፍች የሚፀናበት ጊዜ)
  የጋብቻ ውል ፈፅሞ፣ ይዟት ያልገባት- ግብረ ስጋ ግንኙነት አብሯት ያልፈፀመ- ወይም አብሯት ኑሮ ያልጀመረ ሰው ከፈታት፣ ፍቺውን በመፈፀሙ ብቻ ከርሱ ትለያለች፡፡ በያዝነው ርዕስ መሰረት ደግሞ እሱ ብቻውን በመስለሙ ብቻ ከርሱ ትለያለች፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ፣ ምእመናትን ባገባችሁና ከዚያም ሳትነኩዋቸው በፊት በፈታችኋቸው ጊዜ ለናንተ በነሱ ላይ የምትቆጥሩዋት ዒዳ ምንም የላችሁም፡፡›› (አል አህዛብ 49)
  የእርጉዝ ሴት ዒዳ፣ ያረገዘችውን በመውለዷ ያበቃል፡፡ ጊዜው ቢረዝምም ቢያጥርም ልዩነት የለውም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹የእርግዝና ባለቤቶችም ጊዜያቸው እርጉዛቸውን መውለድ ነው፡፡›› (አል ጠላቅ 4)
  እርጉዝ ያልሆነችና የወር አበባ የምታይ ሴት ዒዳዋ ከተፈታች በኋላ ወይም ባል ከሰለመ በኋላ ሦስት ሙሉ የወር አበባ ማየት ነው፡፡ የወር አበባ ደም መጥቶባት ትጸዳለች፤ ከዚያም በድጋሚ ይመጣባትና ትጸዳለች፤ ከዚያም ለሦስተኛ ጊዜ ይመጣባትና ትጸዳለች፤ ሦስት ሙሉእ የወር አበባ ጊዜ የሚባለው ይህ ነው ፡፡ በወር አበባዎቹ መሐከል ያለው ጊዜ ቢረዝምም ባይረዝምም ልዩነት አይኖረውም፡፡ ይህች ሴት ከሦስተኛው የወር አበባ መጽዳት በኋላ ከታጠበች ዒዳዋ ያበቃል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹የተፈቱ ሴቶችም ነፍሶቻቸውን (ከማግባት) ሦስትን ቁሩእ (ሦስትን አደፍ ወይም ሦስትን የአደፍ ጥራት) ይጠብቁ፡፡›› (አል በቀራ 228)
  ያልደረሰች ሕፃን በመሆኗ፣ ወይም ዕድሜዋ በመግፋቱ፣ ወይም ባለባት ዘውታሪ በሽታ ምክንያት የወር አበባ የማታይ ሴት፣ ከተፈታችበት ጊዜ፣ ወይም ባሏ ከሰለመበት ጊዜ አንስቶ ሦስት ወራቶችን ትጠብቃለች፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ከሴቶቻችሁ ከአደፍ ያቋረጡት (በዒዳቸውሕህግ) ብትጠራጠሩ ዒዳቸው ሦስት ወር ነው፤ እኒያም ገና አደፍን ያላዩት (ዒዳቸው እንደዚሁ ነው፡፡)›› (አል ጠላቅ 4)

ሚስት ካልሰለመች

 • የመጽሐፍት ባለቤት -አይሁድ ወይም ክርስቲያን- ነች?
  • አዎን => ጋብቻው በነበረበት ይቀጥላል፤ ማደስ አይፈልግም፤ ወንድየው ለሚስቱ ተስማሚ በሆኑ መንገዶች ሁሉ በመጠቀም ጥሪ ሊያደርግላት ይገባል፡፡
  • አይቻልም(በፍፁም) => አይደለችም፡ የመጽሀፍት ባለቤት ካልሆነች በመጀመሪያ ወደ ኢስላም ጥሪ ያደርግላታል፤ ከዚያም በዒዳ ወቅት ኢስላምን ተቀብላለች ወይስ አልተቀበለችም ማለትን እናያለን፡፡
   • አዎን => እሷ በኢስላም ውስጥም ሕጋዊ ባለቤቱ ናት የጋብቻቸውን ውል ማደስ አያስፈልግም፡፡
   • አይቻልም(በፍፁም) => የዒዳዋ ወቅት እስከሚያበቃ ድረስ ኢስላምን ለመቀበል ፍቃደኛ ካልሆነች፣ የጋብቻው ውል ይፈርሳል፤ በሰለመች ጊዜ በአዲስ የጋብቻ ውል ሊጋቡ ወይም ሊማለሱ ይችላሉ፡፡