ከሰለሙ በኋላ ስም መቀየር የተወደደ ተግባር ነውን?

ከሰለሙ በኋላ ስም መቀየር የተወደደ ተግባር ነውን?

በመሰረቱ አንድ ሰው ሲሰልም የነበረውን ስም ሳይቀይር በነበረው ስሙ መጠራት አለበት፤ በሠሐባ ዘመን ስምን መለወጥ ወይም መቀየር በሰፊው የሚታወቅ ጉዳይ አልነበረም፤ ብዙ ሰዎች ሰልመዋል፤ ግን በነበራቸው ዐረብኛ ባልሆነ ስማቸው ሲጠሩ ነበር፡፡ ነገር ግን መጥፎ መልዕክትን ያዘለ ከሆነ ባዘለው መጥፎ መልክት ምክንያት ስሙ ይቀየራል፡፡

በሚከተሉት ሁኔታዎች ስምን መቀየር ግዴታ ይሆናል፡

 1. ከአላህ ሌላ ላለ አካል ተገዢነትን የሚያመለክት ከሆነ ወይም ከኢማን ጋር የሚፃረር የሆነ መልክትን የያዘ ከሆነ ይቀየራል፡፡ ለምሳሌ፡ ስሙ ገብረ እገሌ፣ መሲሕ፣ ወይም ገብረ ነብይ፣ ወይም የዚህ ዓይነት ከሆነ ወይም የስሙ ትርጉምና መልዕክት ከኢማን ጋር የሚቃረንና የሚጋጭ ከሆነ ይቀየራል፡፡ ለምሳሌ ሹኑዳ «የአላህ ልጅ» ማለት ነው፤ አላህ ከእንዲህ ዓይነቱ ፍፁም የላቀና የጠራ ነው፡፡ ወይም በአላህ ልዩ ባህሪያቶችና መጠሪያዎች መሰየም ለምሳሌ፣ ንጉሠ ነሥትና የመሳሰሉት የማዕረግ መጠሪያዎች፣ አላህን ብቻ ገላጭ የሆነን ነገር ወደ ባሪያው የሚያስጠጋ የሆነ ስያሜ ይቀየራል፡፡
 2. መጥፎ መልዕክትን ያዘለ ወይም በተፈጥሮ ማንኛውም ጤናማ ነፍስ የሚጠላውና የሚያወግዘው የሆነ መጠሪያ ከሆነ ይቀየራል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ከምግብና ከመጠጥ፣ እንዲሁም በሕይወታችን ውስጥ ከሚያጋጥሙን ጉዳዮች መጥፎና ጎጂ የሆኑትን እርም አድርጎብናል፡፡ ስለሆነም ከኢስላም በኋላ መጥፎ ትርጓሜ ባላቸው ስያሜዎች መጠራት አይፈቀድም፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፤ከእምነት በኋላ የማመጥ ስም ከፋ፡፡›› (አል ሁጁራት 11)
 3. ስያሜው ሙስሊም ባልሆኑ ሕዝቦች ዘንድ ሃይማኖታዊ መልዕክት ያዘለ ከሆነ ወይም ሙስሊም ባልሆኑ ሃይማኖተኞች ዘንድ የሃይማኖታቸው መገለጫ ተደርጎ በሰፊው የሚታወቅ ከሆነ ይቀየራል፡፡ ለምሳሌ፡ ጴጥሮስ፣ ጊዮርጊስ፣ ዮሐንስ፣ ጳውሎስ እና የመሳሰሉት ክርስቲያኖች ዘንድ በሰፊው የሚታወቁ ስሞች ይቀየራሉ፡፡ ይህን ዓይነቱን ስያሜ ምንም ዓይነት መሰል መልዕክትን ያላዘለ ወደ ሆነ ስያሜ መቀየር አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም በኢስላማዊ ሕግ መሰረት፣ እራስን ለጥራጣሬ የሚያጋልጡ ነገሮችን መራቅ ግዴታ ስለሆነና በዚህ ዓይነቱ ስሞች መጠራት ከካሃዲያን ጋር ስለሚያመሳስል ነው፡፡

ለሚከተሉት ነገሮች ስምን መቀየር የተወደደ ተግባር ነው፡፡

አዲሱ ስያሜ አላህ ዘንድ ተወዳጅ ከሆነ፤ ለምሳሌ ይጠራበት የነበረን ስም ወደ ዐብደላህ ወይም ዐብዱረህማን እንዲሁም ለአላህ ባርነትን ገላጭ ወደሆነ ስም ከሆነ፣ እነኚህ ስሞች የሚወደዱ ስያሜዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህ ወደ ኢስላም ከመግባት ጋር ምንም ዓይነት ትስስር የለውም፡፡

 • ያለ ምንም ምክንያት ስምን መቀየርም ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ዐረብኛ ያልሆነ ስሙን ወደ ዐረብኛ መቀየር ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ የሚወደድ ተግባር ነው አይሰኝም፡፡ ወደ ኢስላ ከመግባት ጋርም ግንኙነት የለውም፤
 • የአንድ መጠሪያ ስም ትርጓሜ ከሃይማኖትና እምነት ጋር ይቃረናልን?
  • አዎን => አዎን፡ ይህ ዓይነቱ ትርጓሜ ያለውን ስም መቀየር ግዴታ ነው፤
  • አይቻልም(በፍፁም) => ከሙስሊሞች ሌላ ባሉ ማህበረሰቦች ስሙ ሃይማኖታዊ መልዕክት አለውን? ወይም ሙስሊም ባልሆኑ ሃይማኖተኞች ዘንድ ይዘወተራልን?
   • አዎን => አዎን፡ አደጋን ለመከላከል ሲባል መቀየሩ አስፈላጊ ነው፡፡ ከመመሳሰል ለመራቅ ሲባልም መቀየሩ አስፈላጊ ነው፡፡
   • አይቻልም(በፍፁም) => ነፍሶች የሚጠሉት የሆነ ትርጓሜን የያዘ ነውን?
    • አዎን => ሰውየው ወደ ኢስላም ከመግባቱ ጋር የሚስማማ በሆነ ጥሩ ትርጓሜ ባለው ስም መቀየሩ ይወደዳል፡፡
    • አይቻልም(በፍፁም) => የተጠቀሱትን ዓይነት ትርጓሜ የያዘ ካልሆነ መቀየሩ ግዴታ አይደለም፤ ኢስላም በተስፋፋባቸው በመጀመሪያዎቹ ክፍለ ዘመናት ውስጥ የነበሩ በርካታ ሙስሊሞች ዐረብ ያልሆኑ ስሞቻቸውን አይቀይሩም ነበር፡፡ ያለ ምክንያትም ቢሆንም አንድ ሰው ስሙን መቀየር ይችላል፡፡ በተለይ ደግሞ ወደ አላህ የሚያስወድዱና ዐብደላህና ዐብዱረሕማን ወደ ሚባሉ ስሞች ለመቀየር አስቦ ከሆነ ስሙን መቀየሩ ተወዳጅ ነው።