ወደ ኢስላም ከተገባ በኋላ ያለው ቤተሰባዊ ሕይወት

አካባቢህና ቤተሰብህ

አንድ አዲስ ሙስሊም ወደ ኢስላም ከገባበት ጊዜ አንስቶ ከሚያውቃቸው ሰዎች እንዲሁም ከሙስሊም ወይም ሙስሊም ካልሆኑ ዘመዶቹ ጋር ያለውን ግንኙነትና ቅርርብ ይበልጥ ማጠናከር አለበት፡፡ ኢስላም እራስን ወደ ማግለልና ወደ ባይተዋርነት የሚጣራ ሃይማኖት አይደለም፡፡

ለሰዎች በጎ መዋልና ከነርሱ ጋር በመልካም ስነ ምግባር መኗኗር፣ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) መልካም ስነ ምግባሮችን ለማሟላት የተላኩበት የሆነውን ሃይማኖት ለሌሎች ከሚያስተዋውቁ መንገዶች ሁሉ በላጩና ውጤታማው ነው፡፡

የላቁ ስነ ምግባሮች በተግባር የሚተረጎምባቸውና የተከበሩ መልካም ግንኙነቶች የሚንጸባረቅባቸው እርምጃዎች የመጀመሪያው ከቤተሰብ ጋር ያለው ግንኙነት ነው፡፡ (ገጽ፣ 213 ተመልከት)

የሚከተሉት መርሆች አንድ አዲስ ሙስሊም ከቤተሰቡ ጋር በሚኖረው ትስስር ሊያውቃቸው የሚገቡ ናቸው፡

ወደ ኢስላም ከተገባ በኋላ ያለው ቤተሰባዊ ሕይወት

ባልና ሚስት በአንድነት ከሰለሙ

ባልና ሚስት አብረው ከሰለሙ የነበራቸው የጋብቻ ውል ወይም ኒካሕ በኢስላምም ይጸናል፤ የጋብቻውን ውል እንደ አዲስ ማደስ አያስፈልጋቸውም፡፡

ግን ይህ የማያካትታቸው ተንጠለው የሚወጡ ሁኔታዎች አሉ፡

  1. ጋብቻውን የፈፀመው በሸሪዓው ማግባት ከማይፈቀድለት(መሓሪሞች) መካከል ከአንዷ ጋር ከሆነ፡ ለምሳሌ ከእናቱ ወይም ከእህቱ ወይም ከአክስቱ ጋር ጋብቻ ፈፅሞ የነበረ ከሆነ፣ ከሰለሙ ጊዜ ጀምሮ እንዲፋቱ ማድረግ የግድ ነው፡፡ (ገጽ፣ 200 ተመልከት)
  2. ሁለት እህትማማቾችን ወይም ሴቷን ከአክስቷ ጋር ወይም ሴቷን ከየሹሜዋ ጋር በአንድነት አግብቶ ከሆነም አንዳቸውን የመፍታት ግዴታ ይኖርበታል፡፡
  3. እሱና ሚስቶቹ በአንድ ላይ ቢሰልሙና የሚስቶቹ ብዛት ከአራት በላይ ቢሆን፣ ከአራት ሴቶች በላይ ስለማይፈቀድለት ከነርሱ መካከል አራቱን መርጦ በማስቀረት የተቀረቱን ይፈታቸዋል፡፡