የልጆች ሃይማኖት (እስልምና)

ሰዎች በሙሉ የሚወለዱት በተፈጥሯዊው እምነት በኢስላም ላይ ነው፡፡ ሌሎች ሃይማኖቶች ወላጆቻቸው በሚያስተምሯቸው ትምህርት ምክንያት በደባልነት የሚገቡባቸው ናቸው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ልጅ ሁሉ የሚወለደው በተፈጥሯዊ እምነት- በኢስላም- ላይ ነው፡፡ ወላጆቹ ግን አይሁድ ወይም ክርስቲያን ወይም እሳት አምላኪ ያደርጉታል፡፡›› (አል ቡኻሪ 1292 / ሙስሊም 2658)

ከካሃዲያን ቤተሰብ ተወልደው በሕፃንነታቸው የሞቱ ልጆች፣ በዚህ ዓለም ከነሱ ጋር የሚኖረን ግንኙነት ልክ ከካሃዲያን ጋር የምናደርገው ዓይነት ነው፡፡ አላህ ሚስጥርንና ከዚያም በላይ የተደበቀን ነገር ዓዋቂ ነው፤ እርሱ ዘንድ አንድም ሰው አይበደለም፡፡ እነኚህ ልጆች በትንሳኤው ቀን ፈተና ያቀርብላቸዋል፤ ይፈተናሉ፤ በዚያ ፈተና ታዛዥ የሆነ ጀነት ይገባል፤ አመጸኛ የሆነ ደግሞ እሳት ይገባል፡፡

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ አጋሪያን ልጆች በተጠየቁ ጊዜ፡- ‹‹አላህ ገና ሲፈጥራቸው ምን ሊሰሩ እንደሚችሉ ያውቃል፡፡›› በማለት መልሰዋል፡፡ (አል ቡኻሪ 1317)

በዱንያ ላይ የካሃዲያን ልጆች ሰልመዋል የምንለው መች ነው?

የሕፃናትን መስለም ለማጽደቅ የተለያዩ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ ይገባሉ፡፡ እነሱም፡

 1. ወላጆች ከሰለሙ፤ ወይም አንዳቸው ከሰለመ፤ ልጅ ከወላጆቹ መካከል በሃይማኖት የተሻለ የሆነውን ይከተላል፡፡
 2. ለሃላፊነት ያልበቃ ወይም ያልጎረመሰ፣ ነገር ግን ክፉና ደጉን የለየ ታዳጊ ሕፃን ከሰለመና ወላጆቹ ካልሰለሙስ? አንድ ነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሲያገለግል የነበረ አይሁድ ታዳጊ ልጅ ከዕለታት አንድ ቀን ታሞ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሊጠይቁት መጡና ከራሱ አጠገብ ቁጭ ብለው ‹‹ስለም›› አሉት፤ የልጁ አባት አጠገቡ ነበርና ልጁ ወደ አባቱ ተመለከተ፤ አባቱም «የቃሲምን አባት ታዘዛቸው» አለው፤ ልጁም ሰለመ ከዚያን ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከልጁ ዘንድ ሲወጡ፣ ‹‹ይህን ልጅ ከእሳት ነፃ ያወጣው አላህ የተመሰገነ ይሁን›› አሉ፡፡ (አል ቡኻሪ 1290)
 • ወላጆቹ በአንድነት ነው የሰለሙት ወይስ አንዳቸው ብቻ ነው የሰለመው?
  • አዎን => አንድ ላይ ነው የሰለሙት፡ እስልምናው ይጸድቃል፤ በሙስሊሞች ሕግና ደንብ መሰረት ይኗኗራል፡፡
  • አይቻልም(በፍፁም) => ከቤተሰቡ ተነጥሎ ለብቻው ነው የሰለመው?
   • አዎን => አዎ፡ የሚናገረውን የሚገነዘብና ክፉና ደጉን የሚለይ ከሆነ በዱንያ ላይ መስለሙ ይጸድቅለታል፡፡ ይህ የኢስላም ሊቃውንት ስምምነት ነው፡፡ በአኼራም ይጠቅመዋል፤ ያድነዋል፤ በሚል ሙስሊሞች በሙሉ በአንድ ድምፅ አጽድቀውታል፡፡
   • አይቻልም(በፍፁም) => የከሃዲያን ልጆች ሲሞቱ፣ እነሱን በተመለከተ በዱንያ ላይ ያለው ግንኙነታችን የሚከናወነው ከከሃዲያን እንዳለን ግንኙነት ዓይነት ነው፡፡ አላህ ሚስጥርና ከርሱም በላይ የተደበቀን ነገር ዐዋቂ ነው፤ ‹‹ጌታህ አንድንም ሰው አይበድልም››፤ እናም የትንሳኤ ቀን ይፈትናቸዋል፤ በፈተናው ለርሱ ታዛዥ የሆነ ወደ ጀነት ይገባል፤ ያመፀ ደግሞ ወደ እሳት ይገባል፡፡