የልጆች መብት

የልጆች መብት

  • ጥሩ እናት ልትሆን የምትችል መልካም ሚስት ለጋብቻ መምረጡ አባት ለልጆቹ ከሚያቀርብላቸው ስጦታዎች ሁሉ በላጩ ነው፡፡
  • ስም ከነርሱ የማይለይ የሆነ መገለጫቸው በመሆኑ፣ ልጆችን በሚያማምሩ ስሞች መሰየም ልጆች በወላጆች ላይ ካላቸው መብት መካከል ነው፡፡
  • በመልካም ስነ ምግባር አንጾ ማሳደግ፣ መሰረታዊ የሃማኖት ጉዳዮችን ማስተማርና ሃይማኖታቸውን እንዲወዱ ማድረግ፡፡

ብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹እያንዳንዳችሁ እረኞች ናችሁ፤ ከጠበቃችሁት ነገርም ተጠያቂዎች ናችሁ፤ በሰዎች ላይ የተሾመ ሹም እረኛ ነው፤ ስለነርሱ ተጠያቂ ነው፤ አባወራ በቤተሰቡ ላይ እረኛ ነው፤ ስለነርሱ ተጠያቂ ነው፤ ሴት በባሏ ቤትና በልጆቹ ላይ እረኛ ነች፤ ስለነርሱ ተጠያቂ ነች፤ ባሪያም በአሳዳሪው ንብረት ላይ እረኛ ነው፤ ስለርሱ ተጠያቂ ነው፤ አዋጅ! ሁላችሁም እረኞቸች ናችሁ፤ ሁላችሁም ስለጠበቃችሁት ነገር ተጠያቂዎች ናችሁ፡፡›› (አል ቡኻሪ 2416 / ሙስሊም 1829) ወላጆች እንደየአስፈላጊነቱና አንገብጋቢነቱ ቅደም ተከተል በማስያዝ ልጆቻቸውን ማነጽ ይኖርባቸዋል፡፡ በመጀመሪያ ከማጋራትና ከፈጠራ አመለካከት የጸዱ ማድረግ፣ ትክክለኛውን የእምነት መሰረት እንዲይዙና ከዚያም አምልኮዎችን፣ በተለይም ሠላትን እንዲሰግዱ ማድረግና ብሎም ጥሩ ስነምግባርንና ስርዓቶችን ሊያስተምሯቸው ይገባል፡፡ ክብርና በጎ የሆነን ሁሉ ሊያሳዩዋቸው ይገባል፡፡ ይህ አላህ ዘንድ ትልቅ ከሚባሉ ስራዎች ነው፡፡

  • ወጪ፡ ወላጅ አባት የወንድም ሆነ የሴት ልጆቹን ወጪ የመሸፈን ግዴታ አለበት፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ችላ ማለትም ሆነ መሳነፍ አይገባውም፡፡ እንደውም እንደችሎታውና አቅሙ በተሟላ መልኩ ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት መጣር ይኖርበታል፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አንድ ሰው የሚያስተዳድረውን መጣሉ ብቻ ከወንጀል በኩል ይበቃዋል፡፡›› (አቡ ዳውድ 1692) ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፣ ሴት ልጆችን በመጠበቅና ለነርሱ ወጪ ማድረግን በተመለከተ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹የነዚህን ሴት ልጆች ጉዳይ የተሸከመና ለነርሱም በጎ የዋለላቸው፣ እነርሱ ለርሱ ከእሳት ግርዶ ይሆኑለታል፡፡›› (አል ቡኻሪ 5649/ ሙስሊም 2629)
  • ወንዶችም ሆኑ ሴቶች በሁሉም ልጆች መካከል ፍትሃዊ መሆን፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አላህን ፍሩ በልጆቻችሁ መካከል ፍትሃዊ ሁኑ፡፡›› (አል ቡኻሪ 2447 / ሙስሊም 1623) ሴቶችን ከወንዶቹ ማስበለጥ እንደማይፈቀድ ሁሉ ወንዶችንም ከሴቶች ማስበለጥም አይፈቀድም፡፡ ይህን ማድረግ አደገኛ ችግርን ይፈጥራል፡፡