የመንገደኛ ሰላት

የመንገደኛ ሰላት

  • መንገደኛ ከቦታ ቦታ በሚዘዋወርበት ወይም ከአራት ቀን ላነሰ ወቅት ጊዚያዊ ቆይታ በሚያደርግበት ስፍራ ሆኖ ባለ አራት ረከዓ ሰላቶቹን ሁለት ረከዓ አድርጎ መስገድ ይወደድለታል፡፡ዙህር ዐሱርና ዒሻን የአገሬ ነዋሪ የሆነ ኢማምን ተከትሎ ካልሰገደ በስተቀር በአራት አራት ረከዓ ምትክ ሁለት ሁለት አድርጎ ይሰግዳል፡፡ እንዲያ ከሆነ ግን ኢማሙን ሊከተልና እንደሱ አራት ረከዓ ሊሰግድ ይገባል፡፡
  • ከፈጅር ሱና በስተቀር የተቀሩትን ተቀጥላ ሱና ሰላቶችን ቢተው ወይም ባይሰግድ ይችላል፡፡
  • ዙህርና ዐስሩን በአንድነት መግሪብና ዒሻን በአንድነት አቆራኝቶ መስገድ ይችላል፡፡ በተለይ በሚዘዋወርበትና በሚሳፈርበት ወቅትና ሁናቴ ላይ ከሆነ የአላህን ህግ ገራገርነት እዝነትና ማጨናነቅ የሌለው መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡