የሚፈቀዱ እንሰሳት የትኞቹ ናቸው?

የሚፈቀዱ እንሰሳት የትኞቹ ናቸው?

ሐራምነታቸው ከቁርኣንና ከሱና ማስረጃ ከተገኘላቸው ውጭ ያሉ ሁሉም እንሰሳት መሰረታቸው የተፈቀደ ነው፡፡

የተከለከሉት የሚከተሉት ናቸው፡

  1. አሳማ፡ በኢስላም ውስጥ አሳማ እርም የተደረገና እርኩስ ነው፡፡ እያንዳንዱ ገላውና አካሉ ከርሱም የሚወጣ ማንኛውም ነገር እርምና ነጃሳ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹በክት፣ ፈሳሽ ደምም፣ የእሪያ (አሳማ) ስጋም … በናንተ ላይ እርም ተደረገ፡፡›› (አል ማኢዳ 3) አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የአሳም ስጋ አሱ እርኩስ ነውና፡፡›› (አል አንዓም 145) እርኩስ ማለት ነጃሳ ማለት ነው፡፡

     በቁርኣንና በሱና ለብቻቸው ተነጥለው የተነገሩት ሲቀሩ እንሰሳትን ካረዱ በኋላ መመገብ ይፈቀዳል፡፡

  2. ማንኛውም አዳኝ ጥርሶች ያሉት አውሬ፡ ይህ ማለት ማንኛውም ስጋ በሊታ አውሬ ለማለት ነው፡፡ እንደ አንበሳና ነብር ያሉ ትላልቆችና ግዙፎች ቢሆኑም አለያም እንደ ድመትና የመሳሰሉ ትናንሾችም ቢሆኑ ፍርዱ ልዩነት የለውም፡፡ ውሻም በዚሁ ስር የሚካተት ነው፡፡
  3. ማደኛ ያላቸው በራሪ አዕዋፍ፡ ይህ ስጋ በሊታ የሆኑ አዕዋፍን በሙሉ የሚመለከት ነው፡፡ ቁራ፣ ንስር አሞራንና የመሳሰሉትን ያካትታል፡፡
  4. ነፍሳት፡ ማንኛውም በየብስ የሚኖሩ ነፍሳትን መብላት አይፈቀድም ምክንያቱም እነርሱ ለመታረድ አይመቹም፡፡ ከነሱ መካከል አንበጣ ለብቻው ተነጥሎ ይወጣል፡፡ እሱን መብላት ይፈቀዳል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ሁለት ሙት ነገሮች ተፈቅደውልናል፤ አሳና አንበጣ፡፡›› (ኢብኑ ማጃህ 3228)
  5. እባብ፣ ዘንዶና አይጥ፡ እነኚህን መብላት ክልክል ነው፡፡ እንድንገላቸው ታዘናል፡፡ ነብዩ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አምስት ነገሮች አጥፊዎች ናቸው፡፡ በሐጅ ትጥቅ ላይ ሆኖም፣ ተፈቶም እነሱን መግደል ይፈቀዳል፡፡ እነሱም፡ እባብ፣ ጥቁር አሞራ፣ አይጥ፣ ተናካሽ ውሻና ቀርጮ፡፡›› (አል ቡኻሪ 3136 / ሙስሊም 1198)
  6. የቤት አህያ፡ ዕቃን ከቦታ ቦታ ለመጓጓዝና ለመጫን የሚገለገሉበት አህያ ነው፡፡

የተፈቀዱ እንሰሳት ዓይነት

ከነዚህ መካከል አላህ የፈቀዳቸው በሁለት ይከፈላሉ፡፡

  •  በበረሃ የሚኖሩ፣ ከሰው ልጅ የሚሸሹ፣ ሰዎች ይዘውት ለማረድ የማይችሉትን የዱር እንስሳ ሕጋዊ በሆነ መንገድ ልናድነው ይፈቀድልናል፡፡
  •  ሌላው ዓይነት ደግሞ ለማዳና በቀላሉ ሊያዝ የሚችል ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ደግሞ በኢስላማዊ አስተራረድ ካልታረደ በስተቀር መመገቡ አይፈቀድም፡፡