የስጋ ዓይነቶች በምግብ ቤትና በልኳንዳዎች የሚገኝ ስጋ

የስጋ ዓይነቶች በምግብ ቤትና በልኳንዳዎች የሚገኝ ስጋ

  1. ሙስሊም ወይም የመጽሐፍቱ ባለቤቶች ያላረዷቸው፣ ቡዲሂስቶች፣ ሂንዶዎች፣ እንዲሁም ሃይማኖት የለሾች ያረዷቸው፣ ያልተፈቀዱና እርም የተደረጉም ናቸው፡፡ ብዙሃኑ ነዋሪቿ ሙስሊም ወይም የመጽሐፍ ባለቤቶች ባልሆነች ሀገር ውስጥ የሚገኙ ምግብ ቤቶችና ልኳንዳዎችም በዚህ ስር ይካተታሉ፡፡ ተቃራኒ የሆነ ብይን እስካልተረጋገጠለት ድረስ ይህ ዓይነቱ ሐራም ነው፡፡
  2. ሙስሊም ወይም የመጽሐፍት ባለቤት የሆነ አራጅ ኢስላማዊውን ሕግ በተከተለ መልኩ ያረደውን መብላት በአንድ ድምፅ የሚፈቀድ ወይም ሐላል መሆኑ የጸደቀ ነው፡፡
  3. አንድ ሙስሊም ወይም የመጽሐፍት ባለቤት የሆነ ሰው ኢስላማዊውን ሕግ ባልተከተለ መንገድ እንስሳው እራሱን ስቶ እንዲሞት፣ ወይም ውሃ ውስጥ ሰጥሞ እንዲሞት የተደረገ እንስሳ ስጋ፡፡ ይህን ዓይነቱን መብላት ክልክል ነው፡፡
  4. አንድ አስተራረድ በማያውቅ የመጽሐፍት ባለቤት በሆነ ግለሰብ ወይም ምግብ ቤትና ልኳንዳ ውስጥ የታረደ፡፡ በመሰረቱ ይህ ዓይነቱም ከነሱ እርድ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡ እናም ምንም እንኳ ሐላል መሆኑ ግልጽ የሆነን ስጋ ፈልጎ መመገቡ በላጭ ቢሆንም፣ እንዲህ ያለውን እርድ መመገብ የተፈቀደ መሆኑን የሚያጸድቅ አስተያየት ትክክል ነው፡፡ ሲመገቡት ግን የአላህን ስም ማውሳት መዘንጋት የለበትም፡፡