የባሕር ምግቦች – የየብስ እንሰሳት

የባሕር ምግቦች

የባሕር ምግቦች ሲባል የሚጠቁመው በውሃ ውስጥ እንጂ የማይኖሩትን እንስሳት ነው፡፡

ባሕር ደግሞ ብዙ ውሃ ያለው ሲሆን እንደ ሐይቅና የመሳሰሉት ብዙ ውሃ ያለባቸው የውሃ ዓይነቶችም በዚሁ ስር ይካተታሉ፡፡

እነኚህ የባሕር ምግቦች፣ እንሰሳት ወይም እጽዋቶች ቢሆኑም የታደኑ ወይም ሞተው የተገኙ ሆነው በጤንነት ላይ ጉዳት የማያስከትሉ ከሆነ እነሱን መመገብ የተፈቀደ ነው፡፡

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹የባሕር ታዳኝና ምግቡ ለናንተም ለመንገደኞችም ተፈቀደ፡፡›› (አልማኢዳ 96)

ታዳኝ ማለት ከነነፍሱ የተያዘ ማለት ነው፡፡ ምግቡ የተባለው ደግሞ ከሞተ በኋላ ባሕር የተፋው ማለት ነው፡፡

 የየብስ እንሰሳት

የየብስ እንሰሳትን መብላት የሚፈቀደው ሁለት መስፈርቶች ከተሟሉ ነው፡፡

  • እነሱን መመገብ የተፈቀደ መሆናቸውና
  • አደናቸው ወይም እርዳቸው ኢስላማዊውን ሕግ በተከተለ መልኩ የተከናወነ መሆኑ ነው፡፡