የታማሚ ሰው ሰላት

የታማሚ ሰው ሰላት

አዕምሮውን እስካልሳተና እራሱን እስካወቀ ድረስ በፈለገው ሁናቴ ላይ ቢሆንም ሰላት በሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፡፡ ነገር ግን እስልምና የሰዎችን ሁኔታና ያለባቸውን ጉዳይ ከግምት አስገብቷል፡፡ ከነዚህ ሁኔታዎች አንዱ ህመም ነው፡፡

ይህን ለማብራራት ያክል፡

  • መቆም የማይችል ወይም መቆም የሚያስቸግረው ወይም ለመቆም የሚያስችለው ፈውሱ የሚዘገይበት የሆነ ህመምተኛ ቆሞ መስገድ ይሻርለታል፡፡ እርሱ የሚሰግደው ቁጭ ብሎ ነው፡፡ቁጭ ማለትም ካልቻለ በጎኑ እንደተጋደመ ይሰግዳል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ ቁመህ ስገድ፡፡ ካልቻልክ ቁጭ ብለህ ስገድ፡፡ ካልቻልክ በጎንህ ተጋድመህ ስገድ አል ቡኻሪ 1066
  • ማጎንበስ (ሩኩዕ) ወይም ሱጁድ ማድረግ ያልቻለ ሰው በሚችለው ልክ ምልክት በማድረግ ይሰግዳል፡፡
  • በመሬት ላይ ቁጭ ማለት የሚቸገር ሰው በወንበርና በመሰል ነገሮች ላይ ቁጭ ብሎ መስገድ ይችላል፡፡
  • በህመም ምክንያት ለእያንዳንዱ ሰላት መጥራራት ወይም ዉዱእ ማድረግ የሚቸገር ሰው ዙህራና ዐሱርን በአንድነት መግሪብና ዒሻን በአንድነት በማቆራኘት መስገድ ይችላል፡፡
  • ሰላት ለመስገድ በህመም ምክንያት ውሃን መጠቀም የማይችል ሰው በአፈር ተየሙም ማድረግ ይችላል፡፡