እባኮትን በመቀበል የስራችንን ማስቀጠል እና ማደግ ለማድረግ እርዳን። አላህ ይስጥዎት።
አንድ ሰው ቀደም ሲል በወለድ የሚገለገል የነበረ ቢሆንና ኢስላምን ቢቀበል፣ የሚሰጠው ብይን ወይም ፍርድ ምንድን ነው?
አንድ በወለድ ውል በመገልገል ላይ የነበረ ሰው ኢስላምን ከተቀበለ፣ ፍርዱ ሁለት መልክ የኖረዋል፡፡
- እርሱ ጭማሪውንና የሚገኘውን ጥቅም የሚወስድ አበዳሪ የነበረ ከሆነ፣ ኢስላምን ሲቀበል፣ ዋናውን ብቻ ነጥሎ በመውሰድ ጭማሪውን ይተዋል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ብትጸጸቱም ለናንተ የገንዘቦቻችሁ ዋናዎች አሏችሁ፡፡ አትበድሉም አትበደሉምም፡፡›› (አል በቀራ 279)
- ጭማሪውን የሚከፍል (ተበዳሪ) ከነበረ ደግሞ፡-
- ከባድ የሆነ ጉዳት የማያደርስበት ከሆነ ውሉን በማፍረስ ከዚህ ፅልመት መውጣት አለበት፡፡
- ውሉን ማፍረሱ ትልቅ ኪሳራን የሚያደርስበት ከሆነ ግን፣ ደግሞ ላይመለስበት ቁርጥ ውሳኔ በማድረግ ውሉን እስከተዋዋለበት ጊዜ ድረስ ይቀጥላል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹ከጌታውም ግሳጼ የመጣለትና የተከለከለ ሰው ለርሱ (ከመከልከሉ በፊት) ያለፈው አለው፡፡ ነገሩም ወደ አላህ ነው (አራጣ ወደ መብላት) የተመለሰው ሰው እነዚያ የእሳት ጓዶች ናቸው እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡›› (አል በቀራ 275)
- አንተ ጭማሪ የምትቀበል አበዳሪ ነህን (ወለድ በዪ) ?
- አዎን => እንግዲውስ ያለምንም ጭማሪ ገንዘብህን ዋናውን ብቻ መውሰድ ይኖርብሃል፡፡
- አይቻልም(በፍፁም) => ተበዳሪ ነህ፤ ግን ያለ አንዳች ከባድ ኪሳራ ውሉን ማፍረስ ትችላለህን?
- አዎን => ምንም ኪሳራ የማያስከትልብህ ከሆነና የምትችል ከሆነ ውሉን ማፍረስ አለብህ፡፡
- አይቻልም(በፍፁም) => ውሉን ማፍረስ የማትችል ከሆነ፣ ወይም በማፍረስህ ምክንያት ትልቅ ጉዳት የሚደርስብህ ከሆነ፣ ደግመህ ላትመለስበት ቁርጠኛ ውሳኔ አድርገህ ውሉን ትጨርሳለህ፡፡

