የነብዩን(ሰ.ዐ.ወ) ከተማ (መዲናን) መጎብኘት መዲና፣ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የመካ ጣዖታዊያን ሲያንገላቷቸው ከመካ ወጥተው የተሰደዱበት ከተማ ነች፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መዲና እንደደረሱ መጀመሪያ ያከናወኑት ሥራ የተከበረውን መስጂዳቸውን መገንባት ነበር፡፡ ይህ መስጂድ የዕውቀትና የኢስላማዊ ጥሪ ማዕከልና በሰዎች መሐከል መልካም ነገርን ማሰራጪያ ጣቢያ ሆኗል፡፡ በሐጅ ስነሥርዓትም ሆነ በሌላ አጋጣሚ የነብዩን(ሰ.ዐ.ወ) መስጂድ መጎብኘት እጅግ የተወደደ ነው፡፡…
