የመብላትና የመጠጣት ስርዓት

  የመብላትና የመጠጣት ስርዓት አላህ ለሰው ልጆች የዋለውን ጸጋ ለማስታወስ፣ ከበሽታዎች ለመጠበቅ፣ ማባከንን እና፣ ድንበር ከማለፍ መጠበቅን ይመስል ዓላማንና አምላካዊ ጥበብን ለማረጋገጥ፣ አላህ (ሱ.ወ) በምግብና መጠጥ ውስጥ ብዙ ስርዓቶችን ደንግጓል፡፡ ከነኚህ ስርዓቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡ በወርቅና ብር ዕቃዎች፣ ወይም የሁለቱ ቅብ በሆኑ ዕቃዎች ላይ መመገብ ክልክል ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት፣…

ሸሪዓዊው አደን

ሸሪዓዊው አደን ሸሪዓዊው አደን የሚፈቅደው፣ ስጋቸው የሚፈቀድ፣ ነገር ግን እነርሱን በቁጥጥር ስር አውሎ መባረክና ማረድ የማይመች የሆኑ እንስሳትን ነው፡፡ ለምሳሌ፡ ስጋ በሊታ ከሆኑት በጫካና በዱር የሚገኙ አዕዋፍ፣ እንዲሁም ሚዳቋ፣ ጥንቸልና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ ለአደን መስፈርቶች አሉት፡፡ ከነርሱም መካከል፡ አዳኙ፣ ጤናማ አዕምሮ ያለው፣ አደንን አስቦ የወጣ፣ ሙስሊም አለያም ከመጽሐፍት ባለቤት የሆነ መሆን…

የስጋ ዓይነቶች በምግብ ቤትና በልኳንዳዎች የሚገኝ ስጋ

የስጋ ዓይነቶች በምግብ ቤትና በልኳንዳዎች የሚገኝ ስጋ ሙስሊም ወይም የመጽሐፍቱ ባለቤቶች ያላረዷቸው፣ ቡዲሂስቶች፣ ሂንዶዎች፣ እንዲሁም ሃይማኖት የለሾች ያረዷቸው፣ ያልተፈቀዱና እርም የተደረጉም ናቸው፡፡ ብዙሃኑ ነዋሪቿ ሙስሊም ወይም የመጽሐፍ ባለቤቶች ባልሆነች ሀገር ውስጥ የሚገኙ ምግብ ቤቶችና ልኳንዳዎችም በዚህ ስር ይካተታሉ፡፡ ተቃራኒ የሆነ ብይን እስካልተረጋገጠለት ድረስ ይህ ዓይነቱ ሐራም ነው፡፡ ሙስሊም ወይም የመጽሐፍት…

ኢስላማዊ አስተራረድ

ኢስላማዊ አስተራረድ ኢስላማዊ መስፈርቶችን ያሟላ እርድ ማለት ነው፡፡ የኢስላማዊው አስተራረድ መስፈርቶች የሚያርደው ግለሰብ ለማረድ ብቃት ያለው መሆን አለበት፡፡ እሱም ሙስሊም ወይም የመጽሐፍት ባለቤቶችን፣ ክርስቲያንና አይሁዳውያንን የሚያካትት ሲሆን እርዱን መምረጥ የሚችልና ስለ እርድ የሚያውቅ መሆን አለበት፡፡ የሚያርድበት መሳሪያ እንደ ቢላዋ ያለ የሚቆርጥ፣ ደም የሚያፈስና ለማረድ ብቃት ያለው መሆን አለበት፡፡ እንሰሳቱን በክብደቱ…

የሚፈቀዱ እንሰሳት የትኞቹ ናቸው?

የሚፈቀዱ እንሰሳት የትኞቹ ናቸው? ሐራምነታቸው ከቁርኣንና ከሱና ማስረጃ ከተገኘላቸው ውጭ ያሉ ሁሉም እንሰሳት መሰረታቸው የተፈቀደ ነው፡፡ የተከለከሉት የሚከተሉት ናቸው፡ አሳማ፡ በኢስላም ውስጥ አሳማ እርም የተደረገና እርኩስ ነው፡፡ እያንዳንዱ ገላውና አካሉ ከርሱም የሚወጣ ማንኛውም ነገር እርምና ነጃሳ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹በክት፣ ፈሳሽ ደምም፣ የእሪያ (አሳማ) ስጋም … በናንተ ላይ…

የባሕር ምግቦች – የየብስ እንሰሳት

የባሕር ምግቦች የባሕር ምግቦች ሲባል የሚጠቁመው በውሃ ውስጥ እንጂ የማይኖሩትን እንስሳት ነው፡፡ ባሕር ደግሞ ብዙ ውሃ ያለው ሲሆን እንደ ሐይቅና የመሳሰሉት ብዙ ውሃ ያለባቸው የውሃ ዓይነቶችም በዚሁ ስር ይካተታሉ፡፡ እነኚህ የባሕር ምግቦች፣ እንሰሳት ወይም እጽዋቶች ቢሆኑም የታደኑ ወይም ሞተው የተገኙ ሆነው በጤንነት ላይ ጉዳት የማያስከትሉ ከሆነ እነሱን መመገብ የተፈቀደ ነው፡፡…

አደንዛዥ እጽ

አደንዛዥ እጽ የሚበቅልም ይሁን በፋብሪካ የተመረተ አደንዛዥ እጽን በአፍንጫ በመሳብም ሆነ በመዋጥ፣ ወይም በመርፌ መልክ በመወጋት መጠቀም ወይም መውሰድ ከታላላቅ ወንጀሎችና ሃጢኣቶች መካከል ነው፡፡ እሱ አዕምሮን የሚጋርድ ከመሆኑም በተጨማሪ የሰው ልጅን ነርቮች ያበላሻል፡፡ አደንዛዥ እጽን የሚያዘወትር ሰው በተለያዩ የነርቭና የመንፈስ በሽታዎች ይጠቃል፡፡ ምናልባትም ለሞቱ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ…

አስካሪ መጠጥና አልኮል

አስካሪ መጠጥና አልኮል ማንኛውም አዕምሮን የጋረደ ወይም ከርሱ ተቀላቅሎ ያሸነፈው ወይም ሸፍኖት ተጽእኖ ያሳደረበት ነገር በሙሉ ኸምር ወይም አስካሪ መጠጥ ነው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ማንኛውም አስካሪ ነገር ኸምር ነው፡፡ ማንኛውም ኸምር ደግሞ ሐራም ነው፡፡›› (ሙስሊም 2003) አስካሪ መጠጡ፣ እንደ ወይን፣ የቴምር እሸት፣ በለስና ዘቢብ ባሉ ፍራፍሬዎች፣ አለያም እንደ ስንዴ፣…

በምግብና መጠጥ ዙሪያ ያሉ መሰረታዊ መመሪያዎች

በምግብና መጠጥ ዙሪያ ያሉ መሰረታዊ መመሪያዎች ምግቦችንና መጠጦችን በተመለከት ያለው መሰረታዊ መመሪያ፡ የሰው ልጅን በጤናው፣ በስነ ምግባሩና በሃይማኖቱ ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ የሆኑ፣ በክልክለነታቸው ለብቻ ተነጥለው የተጠቀሱት ነገሮች ሲቀሩ ሌሎቹ ሁሉ የተፈቀዱ መሆናቸውን የሚናገር ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እርም ካደረጋቸው ነገሮች በስተቀር በምድር ላይ ያሉ ነገሮችን ሁሉ ለሰው ልጆች የፈጠረላቸው መሆኑ አላህ…