ተፈጥሯዊ ፈለጎች

ተፈጥሯዊ ፈለጎች ተፈጥሯዊ ፈለግ ምን ማለት ነው?  ኢስላም አንድ ሙስሊም ባማረ ግርማ ሞገስ ላይ እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ ተፈጥሯዊ ፈለግ ማለት አላህ (ሱ.ወ) የሰው ልጅን የፈጠረበት መገለጫዎች ማለት ነው፡፡ አንድ ሙስሊም እነኚህን ነገሮች በመፈፀሙ ሙሉዕ የሚሆንባቸው ናቸው፡፡ ይህን በማድረጉ ያማረ ገጽታና የተዋበ ግርማ ሞገስ ይኖረዋል፡፡ ስለሆነም ኢስላም እነኚህን የውበትና የቁንጅና መሰረት የሆኑ…

ከሰለሙ በኋላ ስም መቀየር የተወደደ ተግባር ነውን?

ከሰለሙ በኋላ ስም መቀየር የተወደደ ተግባር ነውን? በመሰረቱ አንድ ሰው ሲሰልም የነበረውን ስም ሳይቀይር በነበረው ስሙ መጠራት አለበት፤ በሠሐባ ዘመን ስምን መለወጥ ወይም መቀየር በሰፊው የሚታወቅ ጉዳይ አልነበረም፤ ብዙ ሰዎች ሰልመዋል፤ ግን በነበራቸው ዐረብኛ ባልሆነ ስማቸው ሲጠሩ ነበር፡፡ ነገር ግን መጥፎ መልዕክትን ያዘለ ከሆነ ባዘለው መጥፎ መልክት ምክንያት ስሙ ይቀየራል፡፡…

የልጆች ሃይማኖት (እስልምና)

ሰዎች በሙሉ የሚወለዱት በተፈጥሯዊው እምነት በኢስላም ላይ ነው፡፡ ሌሎች ሃይማኖቶች ወላጆቻቸው በሚያስተምሯቸው ትምህርት ምክንያት በደባልነት የሚገቡባቸው ናቸው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ልጅ ሁሉ የሚወለደው በተፈጥሯዊ እምነት- በኢስላም- ላይ ነው፡፡ ወላጆቹ ግን አይሁድ ወይም ክርስቲያን ወይም እሳት አምላኪ ያደርጉታል፡፡›› (አል ቡኻሪ 1292 / ሙስሊም 2658) ከካሃዲያን ቤተሰብ ተወልደው በሕፃንነታቸው የሞቱ ልጆች፣…

ሴቷ ሰልማ ባሏ ባይሰልም ፍርዱ ምንድን ነው?

ሁለት ባልና ሚስቶች አብረው ከሰለሙ፣ እንደ ወንድምና አጎት በኢስላም ሊጋቡ የማይፈቀድላቸው ካልሆኑ በስተቀር የጋብቻቸው ውል ባለበት ይጸናል፡፡ (ገጽ፣ 199 ተመልከት) ሴቷ ሰልማ ባልየው ኢስላምን ለመቀበል ፈቃደኛ ካልሆነ፣ በመስለሟ ብቻ የጋብቻው ውል ወደ ምርጫ ይቀየራል፤ ማለት ሚስት የመምረጥ መብት ይሰጣታል፡፡ የባሏን መስለም በትዕግስት መጠበቅ፡፡ የተለያዩ መንገዶችን በመጠቀም ለባለቤቷ የኢስላምን እውነታ ማብራራትና…

እርሱ ሰልሞ ሚስቱ ባትሰልም የሚኖረው ድንጋጌስ ምንድነው?

በዚህ ጊዜ የሴቷ ሃይማኖት ግምት ውስጥ ይገባል፤ የመጽሐፍት ባለቤት፣ ማለትም አይሁድ ወይም ክርስቲያን ልትሆን ትችላለች፤ አለያም እንደ ቡድሂዝም ሂንዱዊዝምና ጣዖት አምላኪያን መጽሐፍት የለሽ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ልትሆን ትችላለች፤ ወይም በሃይማኖት የማታምን ሃይማኖት አልባ ልትሆንም ትችላለች፡፡ እና ፍርዱ ምንድን ነው? የመጽሐፍት ባለቤት ሃይማኖት ተከታይ የሆነች ሚስት አንድ ሰው ቢስልምና ሚስቱ ግን…

ወደ ኢስላም ከተገባ በኋላ ያለው ቤተሰባዊ ሕይወት

አካባቢህና ቤተሰብህ አንድ አዲስ ሙስሊም ወደ ኢስላም ከገባበት ጊዜ አንስቶ ከሚያውቃቸው ሰዎች እንዲሁም ከሙስሊም ወይም ሙስሊም ካልሆኑ ዘመዶቹ ጋር ያለውን ግንኙነትና ቅርርብ ይበልጥ ማጠናከር አለበት፡፡ ኢስላም እራስን ወደ ማግለልና ወደ ባይተዋርነት የሚጣራ ሃይማኖት አይደለም፡፡ ለሰዎች በጎ መዋልና ከነርሱ ጋር በመልካም ስነ ምግባር መኗኗር፣ ነቢዩ(ሰ.ዐ.ወ) መልካም ስነ ምግባሮችን ለማሟላት የተላኩበት የሆነውን…

ቤተሰብን መጣራት (ወደ ኢስላም መጣራት)

አላህ ኢስላምን እንዲቀበል የቸረው ሰው፣ ቤተሰቦቹንና የቅርብ ዘመዶቹን ወደ ኢስላም የመጥራት ከፍተኛ ጉጉት ሊያድርበት ይገባል፡፡ ምክንያቱም እነርሱ ከማንም በላይ ለርሱ ቅርቦቹና ወዳጆቹም በመሆናቸው ነው፡፡ ለዚህም ከነርሱ የሚደርስበትን ስቃይና እንግልት በትግስት ማሳለፍ አለበት፡፡ የተለያዩ በብልሃት የተሞሉ መንገዶችን መጠቀም ይኖርበታል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡- ‹‹ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፤ በርሷም ላይ ዘውትር፡፡›› (ጧሃ 132)…

የትክክለኛ ዳዕዋ(ጥሪ) መገለጫዎች (ወደ ኢስላም መጣራት)

አላህ(ሱ.ወ)፣ ትክክለኛ ጥሪ ከሌላ የጥሪ ዓይነት የሚለይበትን ባህሪ አብራርቷል፡፡ ትክክለኛ ጥሪ የሚከተሉት መገለጫዎች አሉት፡፡ መረጃና ዕውቀት አንድ ተጣሪ ወይም ዳዒ ወደርሱ በሚጠራበት ነገር ዕውቀት ሊኖረው ይገባል፡፡ የሚናገረውን ነገር ጠንቅቆ የሚያውቅ መሆን አለበት፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ለነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ይላቸዋል፡- ‹‹በል፤ይህች መንገዴ ናት፤ ወደ አላህ እጠራለሁ፤ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ…

ወደ አላህ መጣራት ያለው ትሩፋት (ወደ ኢስላም መጣራት)

ወደ አላህ መጣራት ትልቅ ችሮታ ካላቸው ስራዎችና ወደ አላህ ከሚያቃርቡ ነገሮች ላቅ ያለው ነው፡፡ ይህንኑ የሚያደንቁና የሚያበረታቱ የቁርኣን አንቀጾችና የሐዲስ ዘገባዎች አሉ፡፡ ከነዚህም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡ ወደ አላህ መጣራት በቅርቢቱ ዓለምም ሆነ በወዲያኛው ዓለም የመዳኛና የስኬት መንገድ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ፣ በመልካም ስራም የሚያዙ፣…

ወደ ቀጥተኛው ጎዳና የመመራትንና የንሠሐን ጸጋ ማመስገን

ወደ ቀጥተኛው ጎዳና የመመራትንና የንሠሐን ጸጋ ማመስገን አንድ ሙስሊም አላህ(ሱ.ወ) በርሱ ላይ ከዋላቸው ጸጋዎች ታላቁ የሆነውን፣ ወደ ቀጥተኛው ጎዳና የመመራትንና የንሠሐን ጸጋ ከሚያመሰግንባቸው መንገዶች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡- ሃይማኖትን አጥብቆ መያዝና ለሚያጋጥሙ ችግሮች ታጋሽ መሆን የድልብ ባለቤት የሆነ ሰው፣ ንብረቱ የወሮበሎችና የዘራፊዎች እጅ እንዳያገኘው ከፍተኛ ጥንቃቄና ጥበቃ ያደርግለታል፡፡ ለጉዳት ከሚዳርጉት…