ኢስላም፣ ልዩ ትኩረት የቸራቸው በገንዘብ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ ያሉ ስነምግባሮች

ኢስላም፣ ልዩ ትኩረት የቸራቸው በገንዘብ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ ያሉ ስነምግባሮች ኢስላም፣ ገንዘብ ነክ ጉዳዮችን በተመለከተ መመሪያና ደንብ እንደዘረጋ ሁሉ፣ በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ ሰዎችም ሊላበሷቸው የሚገቡትን በርካታ ስነምግባሮችና ስርዓቶችን በመዘርዘር ልዩ ትኩረት ችሯቸዋል፡፡ ከነዚህም መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡- ታማኝነት፡ ታማኝነት፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር በሚኖረን የንግድ ግንኙነት ወሳኝ ስነ ምግባር ነው፡፡ አንድ ሙስሊም፣…

ቁማር

ቁማር ቁማር ማለት ምንድን ነው? ቁማር ሁለት ተጫዎቾች ወይም ተወዳዳሪዎች ወይም ተወራራጆች አንዳቸው ካተረፈ (ካሸነፈ) ከከሰረው (ከተሸነፈው) ላይ ገንዘብ እንዲወስድ ቅድመ መስፈርት በሚቀመጥለት ውድድርና ጫወታ ላይ ይከሰታል፡፡በዚህ ላይ የሚሳተፉት ሁለቱም ወገኖች ገንዘቡን ከሌላው ወገን በሚያገኙበት ወይም ለሌላው በማስረከብ በሚከስርበት መሀል የሚሽከርከሩ ናቸው፡፡ የቁማር ሸሪዓዊ ፍርድ፡ ቁማር እርም ነው፡፡ በቁርኣንና በነብዩ…

በደልና የሰዎችን ገንዘብ አላግባብ መውሰድ

በደልና የሰዎችን ገንዘብ አላግባብ መውሰድ መጠኑ ቢያንስም የሰዎችን ገንዘብ በግፍ መውሰድ ከከባባድ ሃጢአቶችና ወንጀሎች መካከል ነው፡፡ በደል ኢስላም ካስጠነቀቃቸው እኩይ ተግባራት መካከል አንዱ ነው፡፡ ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹በደል የትንሳኤ ቀን ጽልመት ነው፡፡›› (አል ቡኻሪ 23215 / ሙሲሊም 2579) ትንሽ ቢሆንም፣ የሰዎችን ገንዘብ ያለ አግባብ መውሰድ ክልክል ነው፡፡ ይህ አላህ(ሱ.ወ) ፈፃሚዎቹን…

ሰውን ማታለልና አለማወቅ

ሰውን ማታለልና አለማወቅ ይህ ሐረግ ማንኛውንም በውስጡ የተወሰነ የማይታወቅ ክፍተት ያለው ነገርን ያዘለ፣ በሁለቱ ውል ፈፃሚዎች (ሻጭና ገዥ) መሐከል ጭቅጭቅና ሙግት እንዲከሰት፣ አለያም አንዱ ሌላኛውን እንዲበድል ምክንያት የሚሆን ተግባርን የሚገልጽ ነገር ነው፡፡ ኢስላም፣ ሙግትን ወይም በደልና ጉዳትን አስቀድሞ ለመከላከል ሲል ማታለልንና ግልጽ አልባነትን እርም አድርጓል፡፡ ይህ ነገር ሰዎች ቢስማሙበትና ቢወዱትም…

አንድ ሰው ቀደም ሲል በወለድ የሚገለገል የነበረ ቢሆንና ኢስላምን ቢቀበል፣ የሚሰጠው ብይን ወይም ፍርድ ምንድን ነው?

 ወለድ፣ የገንዘብ በረከት እንዲታጣና የኢኮኖሚ ውድቀት እንዲከሰት ምክንያት ይሆናል፡፡ አንድ ሰው ቀደም ሲል በወለድ የሚገለገል የነበረ ቢሆንና ኢስላምን ቢቀበል፣ የሚሰጠው ብይን ወይም ፍርድ ምንድን ነው? አንድ በወለድ ውል በመገልገል ላይ የነበረ ሰው ኢስላምን ከተቀበለ፣ ፍርዱ ሁለት መልክ የኖረዋል፡፡ እርሱ ጭማሪውንና የሚገኘውን ጥቅም የሚወስድ አበዳሪ የነበረ ከሆነ፣ ኢስላምን ሲቀበል፣ ዋናውን ብቻ…

ወለድ በማህበረሰብና በግለሰቦች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት

ወለድ በማህበረሰብና በግለሰቦች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ኢስላም በማህበረሰብና በግለሰብ ደረጃ በሚያስከትለው ጉዳትና ክስረት የተነሳ በወለድ ዙሪያ ጠበቅ ያለ አቋም ይዟል፡፡ በሀብት መከፋፈል ተግባር ላይ በሀብታሞችና በድሆች መካካል ልዩነትን ይፈጥራል ወለድ፣ ገንዘብ ከማህበረሰቡ ውስጥ በተወሰኑ ሰዎች እጅ ብቻ እንዲኖር የሚያደርግ ሲሆን በርካቶችን የገንዘብ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ያደርጋል፡፡ ይህ ደግሞ በገንዘብ ክፍፍል ላይ…

የወለድ ቅጣት

የወለድ ቅጣት በወለድ የሚገለገል ሰው ከአላህና ከመልክተኛው ጋር ጦርነት በማወጅ እራሱን አጋፍጧል፡፡ በዚህም የአላህ እና የመልክተኛው ተዋጊ ጠላት ይሆናል፡፡ አላህ (ሱ.ወ) አራጣን የሚበሉ ሰዎችን እንዲህ ይላል፡- ‹‹(የታዘዛችሁትን) ባትሰሩም ከአላህና ከመልክተኛው በኾነች ጦር (መወጋታችሁን) ዕወቁ፡፡ ብትጸጸቱም ለናንተ የገንዘቦቻችሁ ዋናዎች አሏችሁ አትበደሉም አትበድሉምም፡፡›› (አል በቀራ 279) ይህ ጦርነት መንፈሳዊና አካላዊ ጫናዎች አሉት፡፡…

የወለድ ፍርድ

የወለድ ፍርድ ወለድ በጥብቅ የተከለከለ እርም(ሐራም) ነው፡፡ እርምነቱም በግልጽ የቁርኣን አንቀጾችና ሐዲሶች ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ወለድ ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል አንዱ ነው፡፡ አላህ (ሱ.ወ) ከወንጀለኞች መካከል ጦርነትን እንዳወጀበት የዛተው ወለድን በሚበላና በርሱ በሚገለግል ሰው ላይ ብቻ ነው፡፡ የወለድ እርምነት በኢስላም ብቻ ሳይሆን በቀደምት መለኮታዊ መመሪያዎችም ጭምር የተደነገገ ነው፡፡ ነገር ግን ከቁርኣን…

ወለድ

ወለድ በወለድ ውስጥ በደልና በሌላው ላይ ጉዳት ማድረስ የሚገኝበት በመሆኑ በኢስላማዊው ሕግ እርም የተደረገ ጭማሪ ገንዘብ ነው፡፡ የወለድ ዓይነቶች ብዙ ናቸው፡፡ ታዋቂዎቹና እርምነታቸው በጣም የጠበቀው፡ የብድርና የእዳ ወለድ ነው፡፡ ይህ በአንድ ገንዘብ ላይ ያለ ሸያጭ ወይም በሁለቱ ጠረፎች መካከል የእቃ ልውውጥ ሳይኖር የሚገኝ ጭማሪ ሲሆን ሁለት መልክ አለው፡፡ የእዳ ወለድ…

ገንዘብ ነክ ትስስር

ገንዘብ ነክ ትስስር አላህ (ሱ.ወ) በምድራዊ የሕይወት ቆይታ ሲሳይን ለመፈለግ መልፋትን ደንግጓል፡ አበረታቷል፡፡ ይህም እንደሚከተለው ተብራርቷል፡፡ አንድ ግለሰብ፣ ስራ የመስራትና በአቅሙ የመንቀሳቀስ ብቃት ካለው ሰዎችን መለመንን ኢስላም ከልክሎታል፡፡ መስራት እየቻለ፣ የመንቀሳቀስ ብቃት እያለው ሰዎችን የሚለምን ሰው፣ ልመናው አላህ ዘንድም ሆነ ሰዎች ዘንድ ያለውን ክብርና ደረጃ እንደሚያሳጣው አስተምሯል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ…