የተባረከው የጾም ፍቺ በዓል

የተባረከው የጾም ፍቺ በዓል በዓላት፣ ከሃይማኖት መገለጫዎች ውስጥ ይመደባሉ፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና በመጡበት ወቅት አንሣሮችን ከዓመቱ ቀናት በሁለት ቀኖች ውስጥ ሲፈነጥዙ፣ ሲጫወቱና ሲደሰቱ አግኝተዋቸው ነበር፡፡ እናም፡ ‹‹እነዚህ ሁለት ቀናት የምን ቀኖቻችሁ ናቸው?›› በማለት ጠየቋቸው፡፡ እነሱም፡ ‹‹ከኢስላም መምጣት በፊት- በጨለማው ዘመን እንደሰትባቸው የነበሩ ቀኖች ናቸው፡፡›› በማለት መለሱ፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ)፡- ‹‹አላህ…

የውዴታ ጾም

የውዴታ ጾም አላህ (ሱ.ወ) እንዲጾም ግዴታ ያደረገው በዓመት አንድ ወርን ብቻ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የቻለና ፍላጎት ያለው፣ ከአላህ ተጨማሪ ምንዳን ለማግኘት የሚከጅል ሰው፣ ሌሎች ቀናትንም እንዲጾም ያበረታታል፡፡ ከነኚህ ቀናት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡- የዐሹራን ቀንና ከርሱ በፊት ወይም በኋላ ያለው ቀን፡፡ የዐሹራ ዕለት የሚባለው በኢሰላማዊው ቀመር መሰረት፣የወርሃ ሙሐረም አስረኛው ቀን ነው፡፡…

በረመዳን ጾሙን ያበላሸ ሰው ፍርዱ ምንድን ነው?

በረመዳን ጾሙን ያበላሸ ሰው ፍርዱ ምንድን ነው? ማንኛውም ያለ በቂ ምክንያት ጾሙን ያበላሸ ሰው፣ ከባድ ወንጀል ፈጽሟል የፈጣሪውን ትዕዛዝ ጥሷል፡፡ ስለዚህም፣ በተውበት ወደ አላህ መመለስ ይኖርበታል፡፡ ጾሙን ያበላሸው በግብረ ስጋ ግንኙነት ካልሆነ፣ ከዚህ ከተውበቱ በተጨማሪ ያንን ጾም የፈታበትን ቀን መክፈል ይጠበቅበታል፡፡ ጾሙን የፈታው በግብረ ስጋ ግንኙነት ከሆነ ግን፣ ያንን ቀን…

አላህ እንዳይጾሙ ፍቃድ የሰጣቸው ሰዎች

አላህ እንዳይጾሙ ፍቃድ የሰጣቸው ሰዎች አላህ (ሱ.ወ) ከሰዎች መካከል ለተወሰኑ ሰዎች በረመዳን ወር አለመጾም እንዲችሉ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡ ይህንንም ያደረገው ለነርሱ ከማዘን፣ ከማግራትና ከማቅለል አንፃር ነው፡፡ እኚህ ሰዎች የሚከተሉት ናቸው:- 1በመጾሙ የሚጎዳ ታማሚ፡- ለርሱ ማፍጠር ይፈቀድለታል፡፡ ከረመዳን በኋላ ሲሻለው ያፈጠረውን ይከፍላል፡፡ . 2 በሽምግልና ወይም ይድናል ተብሎ በማይከጀል በሽታ ምክንያት መጾም…

ጾምን የሚያበላሹ ነገሮች

ጾምን የሚያበላሹ ነገሮች ጾምን የሚያበላሹ ነገሮች፣ አንድ ጾመኛ ሊከለከላቸውና ሊቆጠባቸው የሚገቡ ነገሮች ናቸው፡፡ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡ መብላትና መጠጣት፡- አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ከጎህ የኾነው ነጩ ክርም ከጥቁሩ ክር (ከሌሊት ጨለማ) ለናንተ እስከሚገለጽላችሁ ድረስ ብሉ ጠጡም ከዚያም ጾምን እስከ ሌሊቱ ድረስ ሙሉ፡፡›› (አል በቀራ 187) ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙ…

የረመዳን ጾም

የረመዳን ጾም የጾም ትርጉም ጾም በኢስላም ያለው ትርጉም፡ ጎሕ ከቀደደበት ሰዓት ጀምሮ፣ ፀሐይ እስክትጠልቅ (የመግሪብ ሠላት አዛን የሚባልበት ወቅት) ድረስ ከምግብ፣ ከመጠጥ፣ ከግብረ ስጋ ግንኙነትና ከሌሎችም ጾምን ከሚያበላሹ ነገሮች እራስን በመቆጠብና በማገድ አላህን መገዛት ነው፡፡ የረመዳን ወር በላጭነት የረመዳን ወር በኢስላማዊው ቀመር ዘጠነኛው ወር ነው፡፡ የረመዳን ወር፣ በኢስላማዊው ቀመር ዘጠነኛው…